ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርን ለማፋጠን፣ የገቢና ወጪ ምርትን ለማጓጓዝ የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ እያስፋፋች መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርን ለማፋጠን፣ የገቢና ወጪ ምርትን ለማጓጓዝ የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ እያስፋፋች መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) ገለጹ

AMN መስከረም 29/2018

ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርን ለማፋጠን፣ የገቢና ወጪ ምርትን ለማጓጓዝ የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታን እያስፋፋች ነው ሲሉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) ገለጹ።

ኤ ኤም ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከዋናው ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ጋር የሚያገናኝ የባቡር ሃዲድ ግንባታ ተጀመሯል።

የባቡር መስመር ግንባታው መሉ በሙሉ በኢትዮ ጅቡቲ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ባለሙያዎች የሚገነባ ሲሆን፤ በስድስት ወራት ለማጠናቀቅ መታቀዱ ተገልጿል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ወደ ትግበራ ምዕራፍ እየገባች ነው። ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ያለመሰረተ ልማት ግንባታ የሚታሰብ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ለዚህም ለባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።

የኤ ኤም ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከዋናው ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ጋር የሚያገናኘውና ዛሬ መሰረተ ድንጋይ የተቀመጠለት የግንባታ ፕሮጀክት የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል። ግንባታው ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ አቅም የሚከናወን መሆኑን ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ በራስ አቅም የተመሰረተ ብልፅግናን የማረጋገጥ ውጥኗ ፍሬ እያፈራ ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ዑማ በበኩላቸው፤ የባቡር ሃዲድ ግንባታ ከዲዛይን ጀምሮ በውሰጥ አቅም ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። አክሲዮን ማህበሩ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ የባቡር መስመር፣ የፈጣን መንገድ እና ሌሎች መሰረተ ልማት ግንባታዎችን በስፋት ለማከናወን ግብ መያዙንም ጠቁመዋል።

ዛሬ ኤ ኤም ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከዋናው ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ጋር የሚያገናኘው ሃዲድ ግንባታ መጀመሩን ገልጸው፤ ስራችን በሌሎች ፕሮጀክቶችም ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኤ ኤም ጂ ሆልዲንግስ ባለቤትና ስራ አስፈጻሚ አብዱልሃኪም መሀመድ እንዳሉት፤ የባቡር ሀዲድ ግንባታው ወደ ኢንዱስትሪው የሚገባውን ጥሬ ዕቃ እንዲሁም ከኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚወጣውን ምርት ለማሳለጥ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል።

መንግሥት የወጪ ንግድን ለማበረታታትና የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚ ግንባታ የጎላ ሚና እንዲጫወት እየተዘረጉ ያሉ ማበረታቻዎች የሚመሰገኑ መሆናቸውን አብራርተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review