ባለፈው ዓመት ብቻ በኢትዮጵያ ላይ 13 ሺ 496 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ተደርገዋል ተባለ

You are currently viewing ባለፈው ዓመት ብቻ በኢትዮጵያ ላይ 13 ሺ 496 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ተደርገዋል ተባለ

AMN-መስከረም 29/2018

በ2017 ዓ.ም ብቻ በኢትዮጵያ ላይ 13 ሺ 496 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታውቋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፣ ከጥቅምት 1 እስከ 30 2018 ዓ.ም የሚከበረውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸውንም ዋና ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል።

በ2016 ዓ.ም 8 ሺህ 854 የነበረው የሳይበር ጥቃት ሙከራ በ2017 ዓ.ም ወደ 13 ሺ 496 ከፍ ማለቱንም የገለጹት ወ/ሮ ትዕግስት ሙከራዎቹ በሀገር ላይ የጎላ ጥቃት ሳያደርሱ መቆጣጠር መቻሉን አብራርተዋል።

የሳይበር ምህዳሩን የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር መጨመርና የግንዛቤ ማነስ ለሙከራው መጨመር ዋናኛ ምክንያቶች መሆናቸውንም ዋና ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል።

6ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የተቋማትን እና የኅብረተሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ለማጎልበት “የሳይበር ደህንነት – የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review