መቀለ 70 እንደርታ የአፍሪካ የክለቦች የእጅኳስ ውድድሩን ነገ ይጀምራል

You are currently viewing መቀለ 70 እንደርታ የአፍሪካ የክለቦች የእጅኳስ ውድድሩን ነገ ይጀምራል

AMN-መስከረም 30/2018 ዓ.ም

በአፍሪካ የክለቦች እጅኳስ ውድድር ኢትዮጵያን በብቸኝነት የሚወክለው መቀለ 70 እንደርታ ጨዋታውን ነገ ያከናውናል።

በሞሮኮ ካዛብላንካ በሚከናወነው 46ኛው የአፍሪካ እጅኳስ ወድድር ላይ መቀለ 70 እንደርታ አምስት ክለቦች በያዘው ምድብ አንድ ላይ ተደልድሏል።

የመጀመሪያ ጨዋታውንም ነገ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ከግብፁ አል አህሊ ጋር የሚያከናውን ይሆናል።

በተመሳሳይ ባለፈው ዓመትም የተሳተፉት መቀለ 70 እንደርታዎች ዘንድሮ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁለት ወር የፈጀ ዝግጅት ማድረጋቸውን ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

በዮናስ ሞላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review