የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አትሌት መሰረት ደፋር የፊታችን እሁድ በሚካሄደው የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ሽልማት ላይ ለመታደም አሜሪካ ገብታለች።
በመርሀግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣የቀድሞ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የአሜሪካ ሴናተሮች፣ ከንቲባዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ።
በየአመቱ ስኬትንና የላቀ ስራ የሰሩ ልዩ ተሸላሚዎች ከስፖርት፣ ከኪነጥበብ፣ ከቢዝነስ ዘርፍ ተመርጠው ላደረጉት በጎ አስተዋፅኦ ሽልማት የሚበረከትላቸው ሲሆን ዘንድሮ በአትሌቲክሱ የኦሊምፒክ እና ዓለም ሻምፒዮና አሸናፊ አትሌት መሰረት ደፋር ትሸለማለች።
አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እስካሁን ለአራት ጊዜያት የተካሄደ ሲሆን ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣የዲባባ ቤተሰብና አትሌት ስለሺ ስህን ፣አትሌት ትዕግስት አሰፋና አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ተሸላሚ እንደነበሩ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።