በመጀመሪያ ሩብ አመት 96 ሺህ 210 ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥራቱ በየነ አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም እየገመገመ ይገኛል።
በመጀመሪያ ሩብ አመት ለ77 ሺ 500 ዜጎች የሰራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ96 ሺ 210 ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ከመቶ በመቶ በላይ ማሳካት መቻሉን የቀረበው ሪፖርት አመላክቷል።
ክህሎት መር የሆነ ዘላቂና አስተማማኝ የስራ እድል ለመፍጠር በስልጠና የዳበረ የበቃና የነቃ ዜጋን ማፍራት የበጀት አመቱ ቁልፍ ተግባር ሆኖ እየተሰራ መሆኑን ያኑሱት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ናቸው።
በቅጥር በማደራጀት፣ በኢንተርፕራይዝ፣ በከተማ ግብርና እና በሌሎች የስራ መስኮች በማሰማራት የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተጠቁሟል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች የክፍለ ከተማና የወረዳዎች የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በራሄል አበበ