የቱሪዝም ኮንፍረንስ መዲናነቷን ያረጋገጠችው አዲስ አበባ

You are currently viewing የቱሪዝም ኮንፍረንስ መዲናነቷን ያረጋገጠችው አዲስ አበባ

‎መስከረም – 30/2018 ዓ.ም

‎አዲስ አበባ ከቅርብ አመታት ወዲህ በብዛት አህጉር አቀፍ እና አለም አቀፍ ሁነቶችን ማስተናገድ ጀምራለች ።

‎ነገር ግን ከዚህ ቀደም ከአፍሪካ ህብረት ጋር ተያይዞ ከሚኖሩ ሁነቶች በዘለለ አለም አቀፍ ኮንፍረንሶች ብዙም የማታስተናግ ከተማ እንደነበረች ይታወቃል ።

‎ይሁን እንጂ መንግስት ለከተሞች እድገት ያለውን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ በመገንዘብ አዲስ አበባን በማስዋብ በከተማዋ የሚካሄዱ ሁነቶችን የምትመጥን ከተማ በማድረግ ውጥኑን አሳክቷል ።

‎ለዚህም ማሳያ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እና በወንዞች ዳርቻ የተሰራው ልማት በግንባር ቀደምነት መጥቀስ ይቻላል ።

‎የእነዚህ ፕሮጀክቶች እውን መሆን አዲስ አበባ በ2017 በጀት አመት ብቻ ከ150 የሚበልጡ አህጉር አቀፍ አለም አቀፍ ሁነቶችን ማስተናገድ መቻሏን የእነዚህ ኘሮጀክቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ እሙን ነው።

‎ይህንን ጉዳይ በተመለከት ኤ ኤም ኤን ዲጅታል የአዲስ አበባ አስተዳደር ቱሪዝም ኮምሽን ኮምሽነር ከሆኑት አቶ ሁንዴ ከበደ ጋር ቆይታ አድርጓል ።

‎አቶ ሁንዴ በመዲናዋ የተካሄዱትን ኮንፍረንሶች በተመለከተ ሲያስረዱ ፣ ከተማዋ ከ150 የሚበልጡ አህጉር አቀፍ እና አለም አቀፍ ሁነቶች ስታስተናግድ በታሪክም የመጀመሪያ መሆኑን በመጠቆም ነው ።

‎ከዚህ ቀደም በመዲናዋ የሚካሄዱ ኮንፍረንሶች ምናልባትም ከአፍሪካ ህብረት ጋር ተያይዞ የሚደረጉ እንደነበር አስታውሰዋል ።


‎እነዚህ ሁነቶችም በዓመት ከ12 የማይበልጡ እንደነበሩ ያስረዱት ኮሚሽነሩ፣ አሁን ይሄ ታሪክ ተቀይሮ ከ150 የሚልቁ ሁነቶችን ማስተናገድ መጀመሩ ትልቅ እምርታ እንደሆነ አስገንዝበዋል ።

‎ለዚህ መሰረት የጣሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና እንደ ሀገር የተሰሩ ትልልቅ መሰረተ ልማቶች መሆናቸውን አመላክተዋል ።

‎መሰረተ ልማቶቹ እነዚህን ሁነቶች መሸከም የሚችሉ መሆናቸውን ጠቅሰው ፣ ከተሰሩት ውስጥ የአድዋ ድል መታሰቢያ የኢትዮጰያን ታሪክ ለቀጣይ ትውልድ ከማሸጋገር ባለፈ ለማይስ እና ለኮንፍረንስ ቱሪዝም ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ነው ኮምሽነሩ ያስረዱት ።



‎ከዚህ በተጨማሪ የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ትልልቅ ኮንፍረንሶች ወደ መዲናዋ እንዲመጡ ትልቅ እድል ከፍቷል ሲሉ አቶ ሁንዴ ገልፀዋል ።
‌‎
አህጉር አቀፍ እና አለም አቀፍ ሁነቶች ለመከናወናቸው በዲፕሎማሲ ረገድ የተሰሩ ስራዎች ለዚህ ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል ።

‎በከተማዋ የተከናወኑ ኮንፍረንስ ቱሪዝም በርካታ ቁጥር ያለው ተሳታፊ ወደ ከተማዋ እንዲመጣ ያስቻለና በኢኮኖሚው ላይ ያለው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል ።

‎ለአብነት ያነሱት በቅርቡ በከተማዋ የተከናወነው 2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ከ25 ሺህ በላይ እንግዶች የተሳተፉበት መሆኑን ጠቅሰዋል ።
‌‎
‎ከዚህ ባለፈም የአገልግሎት ዘርፉን ከማዘመን እና ከማበረታታት አንፃር ከፍተኛ እንደሆነና ይህም የግሉን ዘርፍ ከማነቃቃት አንፃር ጉልህ ሚና እንደነበረው ገልፀዋል ።

‎ከዚህ ባሻገር የከተማዋን መልካም ገፅታ ከመገንባት አኳያ ያለው ፋይዳ በጣም ትልቅ መሆኑን አቶ ሁንዴ ገልፀዋል ።

‎የከተማዋ የቱሪዝም መዳረሻዎች ፣ የተሰሩ ትልልቅ ልማቶች የኮንፍረንስ ቱሪዝምን ከማነቃቃት አኳያ ከሌሎች ጊዜያት በተለየ ሁኔታ ሰፊ ልምዶች የተወሰደበት እንደነበር ኮምሽነሩ አስረድተዋል ፡፡
‌‎
‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review