የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዴት ይከሰታል?

You are currently viewing የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዴት ይከሰታል?
  • Post category:ጤና

AMN – ጥቅምት 02 /2018 ዓ/ም

የቫይታሚን ዲ እጥረት ማለት በሰውነት ውስጥ በቂ የቫታሚን ዲ ንጥረ ነገር አለመኖር ነው፡፡

ቫይታሚን ዲ በሰውነታችን ውስጥ ለአጥንት እድገትና ጥንካሬ አስፈላጊ ንጥረ ነገር ሲሆን፤ በዋናነትም በነርቭ እና በጡንቻ ሥርዓት እንዲሁም በበሽታ መከላከል ስርዓታችን ላይ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል።

በቂ የቫይታሚን ዲ ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ካልኖረ በአጥንት እና በጡንቻ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግርን ያስከትላል፡፡

የሥነ ምግብ ህክምና ባለሙያ የሆነችው ኬብሮን ሠናይ የቫይታሚን ዲ እጥረትን በተመለከተ ከኤ.ኤም.ኤን ጋር ባደረገችው ቆይታ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥታለች፡፡

በአብዛኛው በእድሜ በገፉ ሰዎች እና በሴቶች ላይ ይከሰታል የነበረው የቫይታሚ ዲ እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ላይ መከሰት መጀመሩን ተናግራላች፡፡

በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ሁሉ የፀሐይ ብርሃንን በማግኘት እና የአመጋገብ ሥርዓትን በማስተካከል የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዳይከሰት ከወዲሁ መከላከል እንደሚቻልም ባለሙያዋ አስረድታለች፡፡

ይህ እንዳይሆን ግን ሰዎች ብዙ ጊዜ ተሽከርካሪ፣ ጃንጥላ እና የቆዳ ቅባቶችን መጠቀማቸው ለፀሐይ ብርሃን ተጋላጭነት ቢኖርም እንኳን፤ በቂ የፀሐይ ብርሃን ሰውነታችው ባለማግኘቱ የቫይታሚን ዲን እንዳያመርት እና እንዳይጠቀም ያደርገዋል፡፡

የቫይታሜን ዲን ከፀሐይ ብርሃን በተጨማሪ ከተለያዩ ምግቦች ማግኘት ቢቻልም እንኳን በሰውነት ውስጥ ያለው የካልሲየም ንጥረ ነገር በቂ መሆን አለበት፡፡

ሰውነት በቂ የካልሲየም ንጥረ ነገር ከሌለው ቫይታሚን ዲን ማምረትም ሆነ መጠቀም አይችልም፡፡

ወተትና የወተት ተዋጽኦዎች፣ አሣ፣ እንቁላል፣ ጥቁር አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች እንደ ሀበሻ ጐመን፣ ብሮክሊን እና ቆስጣ፣ ከቅባት እህል ሰሊጥን እና የመሳሰሉ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ የተሻለ የካልሴየም መጠን በሰውነታችን ውስጥ እንዲኖረን ይረዳል፡፡

ሰውነታችን በቂ የካለሲየም መጠን ካለው ደግሞ ቫይታሚ ዲን በጥሩ ሁኔታ ማምረትና መጠቀም ስለሚችል የቫይታሚን ዲ እጥረትን መከላከል ይቻላል፡፡

የቫይታሚን ዲ እጥረት ምንም አይነት የበሽታ ምልክት ላያሣይ ይችላል ወይም ምልክቶቹ ለመታየት ብዙ ዓመታት ሊወስዱ ይችላሉ። ይሁን እንጂ የረጅም ጊዜ የጤና ችግሮች አደጋን ሊጨምሩ እንደሚችሉ ይታመናል፡፡

ሰውነት በቂ የፀሐይ ብርሃን እንዲያገኝ በማድረግ እና የአመጋገብ ሥርዓትን በማስተካከል የአጥንት እና የጡንቻ ጤናን ማሳደግ፣ የበሽታ መከላከል ስርዓትን ማስተካከል፣ የሕዋስ እድገትን ማገዝ፣ የደም ግፊትን መቆጣጠር እና የልብና የደም ቧንቧ ጤናን ማስተካከል እንደሚቻል የሥነ-ምግብ ባለሙያዋ ኬብርን ሠናይ ሙያዊ ምክሯን ለግሳለች፡፡

በ በረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review