የስፖርት ማዕከላቱ ጤናን ለመጠበቅ ፣ ተተኪ ስፓርተኞችን ለማፍራት የሚያግዙ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

You are currently viewing የስፖርት ማዕከላቱ ጤናን ለመጠበቅ ፣ ተተኪ ስፓርተኞችን ለማፍራት የሚያግዙ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

AMN- ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም

የስፖርት ማዕከላቱ ጤናን ለመጠበቅ ፣ ተተኪ ስፓርተኞችን ለማፍራት የሚያግዙ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በመዲናችን አዲስ አበባ ነዋሪዎች ስፓርታዊ እንቅስቃሴን ባህል ፣ የአኗኗር ዘይቤ ፣ ጤናን መጠበቂያ ፣ ማህበራዊ ግንኙነትን ማጎልበቻ መንገድ እያደረጉት ይገኛል ብለዋል።

በየእለቱ በተለይም በእረፍት ቀናት ህፃናት ፣ ወጣቶች ፣ አረጋዉያን በተናጠል እና በጋራ የተለያዩ ስፓርታዊ እንቅስቃሴዎችን በመኖሪያ አካባቢ እና ከትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ በሆኑ መንገዶች ሲያከናዉኑ መመልከት የተለመደ ሆኗል ።

ማዕከላቱ ጤናን ለመጠበቅ ፣ ተተኪ ስፓርተኞችን ለማፍራት የሚያግዙ በመሆናቸዉ ህብረተሰባችንም ወደ ማዕከላቱ በመሄድ ስፓርታዊ እንቅስቃሴዎች የማድረግ ልምምዱን ይበልጡን ማሳደግ ይገባዋል ሲሉ አሳስበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review