በከተማዋ የተከናወኑ ሁነቶች እና አበይት የአደባባይ በዓላት ስኬት ከህዝቡ ጋር በጋራ በመሰራቱ የተገኘ ውጤት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

You are currently viewing በከተማዋ የተከናወኑ ሁነቶች እና አበይት የአደባባይ በዓላት ስኬት ከህዝቡ ጋር በጋራ በመሰራቱ የተገኘ ውጤት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

AMN- ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል ፡፡

በጉባኤው የተለያዩ የምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ያሉትን ጥያቄና አስተያየት አቅርበዋል ፡፡ የምክር ቤት አባላት ያቀረቧቸውን ጥያቄ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ ፡፡

አዲስ አበባ ላይ በተሰሩና እየተሰሩ ባሉ የኮሪደር ልማት ከተማዋ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤዎችን የማዘጋጀት ዓቅሟ እያደገ መጥቷል፤ በእነዚህ ጉባኤዎችና በመስከረም ወር የተከናወኑ ዓበይት የአደባባይ በዓላት በከተማዋ የተከናወኑበት ወር ሲሆን እነዚህ ሁነቶች በድምቀት ተከብረው አልፈዋል ለዚህ ሰኬት የተሰሩ ስራዎች ምንድናቸው ለሚለው የምክር ቤት አባላት ጥያቄ ከንቲባዋ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ለበዓላቱና ለሁነቶቹ ስኬት ከህዝቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ግልፅነት በመፍጠር ወደ ስራ መገባቱን ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገለፁት፡፡ በተለይ በተከናወኑ ጉባኤዎች፣ ሆቴሎች የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ እና ክፍያን ተመጣጣኝ በማድረግ ላደረጉት ትብብር ምስጋና ይገባል ሲሉ ከንቲባዋ ገልፀዋል፡፡

ህዝቡ አጠቃላይ እንግዶቹን በኢትዮጵያዊ አንግዳ ተቀባይነት ያደረገው ተሳትፎ የሚደነቅ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ በከተማዋ የተከናወኑ ሁነትና የአደባባይ በዓላት አብሮነትን እና አንድነትን በተግባር ያሳዩ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ህዝቡ መሰረተ ልማቶች የኔ ናቸው ብሎ በመንቀሳቀሱ በከተዋማ በተከበሩ በርካታ ዓበይት በዓላት እና ሁነቶች አንድም የተበላሸ የኮሪደር ልማት አለመኖሩን የገለፁት ከንቲባዋ ይህም በሌሎቹ ስራዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በ- ያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review