የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ቀዳሚዉ ጥያቄ ልማት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ቀዳሚዉ ጥያቄ ልማት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘምን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን በአድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አደራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባኤው የምክር ቤት አባላቱ ከመረጣቸው ህዝብ ጋር ባደረጉት የመራጭ ተመራጭ ውይይት ምላሽ ያስፈልጋቸውል ተብለው የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አቅርበዋል ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤም ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰጡት ማብራሪያ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው እና የሚጠይቀው የልማት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በህዝቡ ከተነሱና ከተጠየቁ ጉዳዮች መካከል የልማት፣ የስራ እድል ፈጠራና ገበያን ማረጋጋት ቀዳሚ መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡

የተነሱት ጥያቄዎችና ሃሳቦች የበለጠ ውጤት እንድናስመዘግብ የሚያግዙ፣ የህዝቡን የዕለት ተዕለት ኑሮ እንድናሻሽል የሚያችሉ ጥያቄዎች ናቸው ብለዋል ከንቲባ አዳነች፡፡

መንግስት የተያዘውን የብልፅግና ግብ የበለጠ በማሳካት፣ ከጊዜው ጋር እያደገና እየሰፋ የሚሂደውን የህዝብ ጥያቄ እያዳመጠ እና ቅድሚያ የሚሰጠውን በማስቀደም በሂደት ይመልሳል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማብራሪያቸው፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review