የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የልዩ ተሸላሚ እውቅና ሰጠ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የልዩ ተሸላሚ እውቅና ሰጠ

AMN – ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ጨምሮ ለ5 ተጠሪ ተቋማት እውቅና ሰጥቷል፡፡

እውቅና ከተሰጣቸው ተቋማት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ልዩ ተሸላሚ ሆናል። ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የ2017 በጀት አመት ላይ ላሳዩት የላቀ አፈጻጸም የተሰጠ እውቅና መሆኑ ተነስቷል። የአዲስ አበባ ከተማ ምከር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር ፣ እንደ ከተማ እና እንደ ሀገር አስተዋጽኦ ያደረጉ ተቋማት እውቅና ተሰጧቸዋል ብለዋል።

በቀጣይም ለተቋማቱ ከእቅናው ባለፈ በቂ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ የላቀ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ይደረጋል ብለዋል አፈ ጉባኤዋ።

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክን ፣ ዋና ኦዲትና መስሪያ ቤት፣ የመሬት ማስለቀቅ እና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤ ፣ የስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና እና የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እውቅና ተሰቷቸዋል።

ለምክር ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት አመት አፈጻጸም ዕውቅናና የ2018 በጀት አመት እቅድ ግቦች ስምምነት ፊርማ ተካሄዷል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review