ሠንደቅ ዓላማችን አለምአቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነታችን የምናሳይበት የማንሰራራት ጉዞ አርማችን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለፁ

You are currently viewing ሠንደቅ ዓላማችን አለምአቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነታችን የምናሳይበት የማንሰራራት ጉዞ አርማችን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለፁ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN- ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

ሠንደቅ ዓላማችን አለምአቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነታችን የምናሳይበት የማንሰራራት ጉዞ አርማችን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለፁ፡፡

18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተከብሯል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ቀኑ ለሠንደቅ አላማችን ልንሰጠው የሚገባውን ክብር የምናድስበት፣ ቃለ ኪዳናችንን የምናፀናበትና ብሄራዊ የአርበኝነት መንፈሳችንን የምናድስበት ታላቅ ዕለት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሠንደቅ ዓላማችን ፈተናዎችን በጽናት ተሻግረን አፍሪካዊት ተምሳሌት ሀገር የመገንባት አቅማችንን የምናጎለብትበት፣ አለምአቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነታችን የምናሳይበት የማንሰራራት ጉዞ አርማችን ነው ብለዋል፡፡

ሰንደቅ አላማችን የውስጥና የውጪ ጠላቶቻችን ሊሰብሩት የማይችሉት የህብረብሄራዊ አንድነታችንና የሉአላዊነታችን ምሽግ ነውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሰንደቅ አላማችን በታሪክ ውጣ ውረዶች ውስጥ የጽናታችን ምልክት ነው ያሉት አፈ ጉባዔው፤ ዛሬም ለሀገራችን ብልፅግናና ዘላቂ ልማት ያለንን ጽኑ አቋም እንዲሁም ወደ ብሩህ የከፍታ ዘመን የተሻገርን መሆናችንን የምናውጅበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በ-በረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review