ፈረንሳይ ነጥብ ስትጥል ፣ ጀርመን እና ቤልጂየም አሸነፉ

You are currently viewing ፈረንሳይ ነጥብ ስትጥል ፣ ጀርመን እና ቤልጂየም አሸነፉ

AMN-ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም

በአውሮፓ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ አራት ላይ የምትገኘው ፈረንሳይ ነጥብ ጥላለች።

ከሜዳዋ ውጪ አይስላንድን የገጠመችው ፈረንሳይ 2ለ2 ተለያይታለች። ለፈረንሳይ ክርስቶፈር እንኩንኩ እና ዦን ፍሊፕ ማቴታ ፣ ለአይስላንድ ደግሞ ቪክቶር ፖልሰን እና ክሪስቲያን ህሊንሰን ኳስ እና መረብን አገናኝተዋል።

የ28 ዓመቱ አጥቂ ማቴታ ለብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል። በዚሁ ምድብ ዩክሬን አዘርባጂያን 2ለ1 ማሸነፍ ችላለች። ፈረንሳይ በ10 ነጥብ ስትመራ ፣ ዩክሬን በሰባት ነጥብ ትከተላለች።

ምድብ አንድ ላይ ጀርመን በኒክ ቮልትማደ ግብ ሰሜን አየርላንድን 1ለ0 አሸንፋለች። ስሎቫኪያም ሉክዘንበርግን 2ለ0 ረታለች። ጀርመን በዘጠኝ ነጥብ ምድቡን ስትመራ ፣ ስሎቫኪያ በእኩል ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጣ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ቤልጂየም በኬቨን ደብሩየና ሁለት የፍፁም ቅጣት ምት ፣ ቶማስ ሙኒር እና ሊአንድሮ ትሮሳርድ ግቦች ዌልስን 4ለ2 ማሸነፍ ችላለች። ድሉን ተከትሎ ቤልጂየም ምድብ 10ን በ14 ነጥብ መምራት ጀምራለች።

በምድብ ሁለት ስዊዘርላንድ ከስሎቬኒያ 0ለ0 ስትለያይ ፣ ስዊድን በሜዳዋ በኮሶቮ ተሸንፋለች። አሌክሳንደር ኢዛክ እና ቪክቶር ዮኬሬሽን የመሰሉ አጥቂዎችን የያዘችው ስዊድን ከአራት ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ አግኝታለች።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review