ኬፕ ቨርድ ኢስዋቲኒን በማሸነፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ መሆኗን አረጋግጣለች።
ከ600 ሺ ያልበለጠ ሕዝብ ያላት ትንሿ ሀገር ካሜሩን ያለችበትን ምድብ አራት በበላይነት ተወጥታለች። በሜዳዋ ኢስዋቲኒን 3ለ0 የረታችው ኬፕ ቨርድ ከ10 ጨዋታ 23 ነጥብ በመሰብሰብ በቀዳሚነት አጠናቃለች።
የሀገሬው ሕዝብም ታሪክ በሰራው ብሔራዊ ቡድን በመኩራት በተለያየ መንገድ ደስታውን እየገለፀ ይገኛል። በዚህ ምድብ በቀላሉ ታልፋለች የሚል ቅድመ ግምት ተሰጥቷት የነበረችው ካሜሩን ከአንጎላ ጋር 0ለ0 ተለያይታለች። 19 ነጥብ በመያዝም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ለማጠናቀቅ ተገዳለች።
በሸዋንግዛው ግርማ