በኬኒያ ፖለቲካ ከፍተኛ ተጽዕኖ የነበራቸው አንጋፋ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ በ80 አመታቸው ህይወታቸው አልፏል።
በህንድ በህክምና ክትትል ላይ የነበሩት ኦዲንጋ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በእግራቸው እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ወቅት ተዝለፍለፈው መውደቃቸው ተዘግቧል።
ሀኪሞች ፖለቲከኛውን ለማዳን ርብርብ ቢያደርጉም ሳይሳካ ቀርቶ ኦዲንጋ በልብ ድካም ህይወታቸው ማለፉን ይፋ አድርገዋል።
ራይላ ኦዲንጋ በኬንያ ፖለቲካ ውስጥ በግንባር ቀደም ከሚጠቀሱ ተቀናቃኞች መካከል አንዱ የነበሩ ሲሆን፤ ከ2008 እስከ 2013 የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆንም አገልግለዋል።
ሆኖም ፖለቲከኛው ሀገሪቱን ለመምራት ለአምስት ጊዜያት በኬንያ ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት ቢወዳደሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
በዳዊት በሪሁን