በንጋት ሐይቅ ላይ 70 የሚደርሱ የወጣት ኢንተርፕራይዞች በዓሳ ማስገር ስራ ተደራጅተው ወደ ሥራ መግባታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

You are currently viewing በንጋት ሐይቅ ላይ 70 የሚደርሱ የወጣት ኢንተርፕራይዞች በዓሳ ማስገር ስራ ተደራጅተው ወደ ሥራ መግባታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

AMN – ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም

በታላቁ የኢትዮጵ ሕዳሴ ግድብ የንጋት ሰው ሰራሽ ሐይቅ ላይ 70 የሚደርሱ የወጣት ኢንተርፕራይዞች በዓሳ ማስገር ስራ ተደራጅተው እየሰሩ እንደሚገኙ የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ – የንጋት ሐይቅ የረቂቅ ማስተር ፕላን ጥናት ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ(ዶ/ር)፤ ሕዳሴ ግድብ የፈጠረው የንጋት ሐይቅ ለበርካታ ዜጎች በረከት መሆን ጀምሯል ብለዋል።

የንጋት ሐይቅ አሁን ላይ በዓመት ከ15ሺህ ቶን በላይ ዓሳ ማምረት የሚያስችል አቅም እንዳለው ጠቅሰው በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ 5ሺህ ቶን የዓሳ ምርት ለገበያ መቅረቡን ገልጸዋል።

የሐይቁን ከፍተኛ የዓሳ ምርታማነት አቅም ለማሳደግ የንጋት ሐይቅ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ዝግጅት የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን እንደሚያግዝም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በንጋት ሐይቅ ላይ ለዓሳ ማስገር ስራ አስፈላጊ መሳሪያዎች የተሟሉላቸው 70 የሚደርሱ የወጣት ኢንተርፕራይዞች ስራ መጀመራቸውንም አስታውቀዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው ለንጋት ሐይቅ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ዝግጅትና ትግበራ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

በሕዳሴ ግድብ የተፈጠረው የንጋት ሐይቅ ላይ በዓሳ ማምረት የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው በርካታ ወጣቶች ሃብትና ጥሪት እያፈሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review