የደመወዝ ጭማሪዉ የኑሮ ሁኔታቸውን ከመደገፉም ባሻገር የስራ ተነሳሽነትን እንደፈጠረላቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች ተናገሩ

You are currently viewing የደመወዝ ጭማሪዉ የኑሮ ሁኔታቸውን ከመደገፉም ባሻገር የስራ ተነሳሽነትን እንደፈጠረላቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች ተናገሩ
  • Post category:ኢኮኖሚ

AMN ጥቅምት 8/2017

መንግስት በቅርቡ የወሰነውና በአጭር ጊዜ ተግባራዊ የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ የኑሮ ሁኔታቸውን እንዲደግፍ ከማድረግ ባለፈ ተጨማሪ የስራ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች ተናገሩ።

የደሞዝ ማሻሻያ ተግባራዊ ሆኖ ለመንግስት ሰራተኛዉ እንዲደርስ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን አዲስ አበባ ከተማ ቀዳሚ በመሆን እስካሁን ባለው ለ10 ተቋማት መከፈሉ ተነግሯል።

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊው አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን እስከ ጥቅምት 15 /2018 ዓ ም በከተማዋ ለሚገኙ ሁሉም የመንግስት ተቋማት ሰራቶች ተከፍሎ እንደሚጠናቀቅ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡

አስተዳደሩ የመንግስት ሰራተኛውን ለመደጎም ከ14ቢሊየን ብር በላይ በመመደብ የተለያዩ የሰራተኛውን የኑሮ ጫና የሚያቀሉ ስራዎችን እየሰራ ነው ያሉት ኃላፊው በዚህ ብቻ ሳይወሰን በስራ አካባቢው ጭምር የተለያዩ ድጋፎች እንደሚደረግለትም አረጋግጠዋል፡፡

የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ ከጠበቁት በላይ መሆኑንና በፍጥነት መድረሱ ደግሞ እንዳስደሰታቸው የተናገሩት ሰራተኞቹ ይህም ለተጨማሪ የቤት ስራና የህዝብ ሃላፊነት እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል፡፡

አስተዳደሩ የመንግስት ሰራተኛውን ብቻ ሳይሆን የሁሉንም የከተማዋ ነዋሪ የኑሮ ጫና ለማቅለል እያደረጋቸው ያሉ ድጎማዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የደሞዝ ጭማሪውን ምክንያት በማድረግ በሸቀጦች እና ሌሎች ምርቶች ላይ ጭማሪ የሚያደርጉ ህገወጥ ነጋዴዎችና አንዳንድ አካላት ላይ የጀመረውን የቁጥጥርና እርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review