የዓይን ድርቀት እንዴት ይከሰታል? ሕክምናውስ?

You are currently viewing የዓይን ድርቀት እንዴት ይከሰታል? ሕክምናውስ?
  • Post category:ጤና

AMN-ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም

በቂ የሆነ የጤና ክትትል ካልተደረገ አይን ይደርቃል።

በዘሀን በደስታ ውሃ የሚያፈልቀው ዓይን፤ የተጻፈለት የተዜመለት የተዘመረለት ዓይን፣ ዓይን እንዴት ሊደርቅ ይችላል..?

በዳግማዊ ሚኒሊክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ልዩ ግርማ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የዓይን መድረቅን በተመለከተ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዓይን የተለያዩ ክፍሎች ሲኖሩት ከውስጠኛው ክፍል ወደ ውጨኛው ክፍል የሚፈሰው እምባ መጠኑ ሲያንስ ወይም ጨርሶ ሲጠፋ ዓይን ደርቋል ተብሎ ብያኔ ይሰጣል ይላሉ፡፡

መንስኤው በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ለረጅም ጊዜ ስራ ላይ መቆየት፣ የእምባ ከረጢት (እጢ) መጎዳት፤ ከፍተኛ ሙቀት እንዲሁም የሚወሰዱ መድኃኒቶች ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ዶ/ር ልዩ ይናገራሉ።

ከዓይን ድርቀት ምልክቶች መካከል ማቃጠልና ምቾት መንሳት ዋንኞቹ ናቸዉ፡፡

ባለሙያው እንደሚሉት በወቅቱ ህክምና ከተደረገለት የዓይን ጤናና ድርቀት ተጨማሪ ጉዳት ሳያስከትል መከላከል ይቻላል፡፡

የእምባ ትነትን ለመከላከል የኑሮ ሁኔታን ማሻሻል ጨምሮ የእምባ ቱቦን በቀዶ ህክምና በመዝጋት ማዳን፤ ሰው ሰራሽ እምባን መተካት፤ በቂ ክትትልና የሙያ ድጋፍ ማግኘት የደረቀን ዓይን ወደነበረበት ለመመለስ ይቻላል ሲሉ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

በአለኸኝ አዘነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review