የመልካ ባሮ ኢሬቻ በዓል በጋምቤላ ከተማ ለአምስተኛ ጊዜ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ይገኛል

በዛሬው “መልካ ባሮ” ኢሬቻ በርካታ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ነው።

የበዓሉ ተሳታፊዎች ውብና ማራኪ በሆኑ ባህላዊ አልባሳትና እሴቶች አሸብርቀው፣ ባህላዊ ጭፈራዎችንና ልዩ ልዩ ዜማዎችን በማዜም ነው በዓሉን እያከበሩ የሚገኙት።

በበዓሉ ላይ አባገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች፣ ቄሮዎችና ቀሬዎች እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋ
ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ሁሉን ነገር ለፈጠረ አምላክ ምስጋና የሚያቀርቡበትና መጪው ዘመን መልካም እንዲሆን ምኞታቸውን የሚገልፁበት በዓል መሆኑን ተዘግቧል።