ፉልሃም ከ አርሰናል፦ መድፈኞቹ መሪነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ጨዋታ

You are currently viewing ፉልሃም ከ አርሰናል፦ መድፈኞቹ መሪነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ጨዋታ

AMN-ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም

የሊጉ መሪ አርሰናል በክራቫን ኮቴጅ ፉልሃምን የሚገጥምበት ጨዋታ ምሽት 1:30 ይከናወናል።

ሁለቱ የለንደን ክለቦች የሚያደርጉት ጨዋታ በትልቁ ይጠበቃል።

መድፈኞቹ በለንደን ደርቢ ያላቸው ክብረወሰን የሚያኩራራ ነው።

ከ2022/23 የውድድር ዓመት ጀምሮ ከሜዳቸው ውጪ ካደረጓቸው 18 የለንደን ደርቢ ጨዋታዎች የተሸነፉት በአንዱ ብቻ እንደሆነ የኦፕታ ቁጥራዊ መረጃ ያሳያል።

በዛሬው ጨዋታ በአርሰናል በኩል ለሳምንታት ከሜዳ የሚርቀው ማርቲን ኦዴጋርድ አይሰለፍም።

ከባየር ሊቨርኩሰን በውሰት የመጣው ተከላካዩ ፒኤሮ ሂንካፒዬ የስብስቡ አካል ሊሆን ይችላል ተብሏል።

አርሰናል ከፉልሃም ጋር ባደረጋቸው የመጨረሻ 14 ጨዋታዎች እጅ የሰጠው በአንዱ ብቻ ነው። ዘጠኙን ጨዋታ በድል ተወጥቷል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review