ኢትዮጵያ እና ጃፓን በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋገጡ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና ጃፓን በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋገጡ

AMN- ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ እና ጃፓን የበጀት ድጋፍ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ እና በኢትዮጵያ የጃፓን ኢንቨስትመንቶች ማስተዋወቅን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማሳደግ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ምክትል ፕሬዚዳንት ናኦኪ አንዶ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከ2025 የዓለም አቀፍፉ ገንዘብ ድርጅት እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በሁለትዮሽ ግንኙነት እና የልማት ትብብር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም አቶ አህመድ ሽዴ፣ ጃፓን በኢትዮጵያ ልማት ያላትን የረዥም ጊዜ አጋርነት እና አስፈላጊ ድጋፍ አጉልተው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የልማት ፍላጎቶችን በተለይም እንደ መሠረተ ልማት፣ ኃይል እና ኢንዱስትሪ ባሉ ቁልፍ ዘርፎች በተሻለ ሁኔታ ለመፍታት፣ የገንዘብ ድጋፍ ማሳደግ እንደሚያስፈልግም አፅንዖት ሰጥተዋል።

የጃይካ ምክትል ፕሬዚዳንት ናኦኪ አንዶ በበኩላቸው፣ ጃፓን ኢንቨስትመንትን ማስተዋወቅ፣ የግሉ ዘርፍ እድገት እና የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽንን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ሁለቱም ወገኖች የበጀት ድጋፍ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ እና በኢትዮጵያ የጃፓን ኢንቨስትመንቶች ማስተዋወቅን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማሳደግ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review