ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በአፍሪካ በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ይፋ አደርጓል፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) መረጃ ሩዋንዳ፣ ኡጋንዳ፣ ኢትዮጵያ፣ ቤኒን እና አይቮሪ ኮስት በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት መካከል ተጠቃሾች ሆነዋል።

አይ ኤም ኤፍ በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ይፋ ባደረገው እትሙ፣ ከሰሃራ በታች ካሉ ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት እያደገ ለሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት በፖሊሲ ማሻሻያ፣ ጥንቃቄ በተሞላበት የፊስካል አስተዳደር እና በመሠረተ ልማት እና በማኑፋክቸሪንግ ኢንቨስትመንት ላይ ላሳዩት ጠንካራ አፈፃፀም እውቅና ሰጥቷል።
በተቃራኒው በአህጉሪቱ ትልቅ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆኑት እንደ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ያሉ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች በአፍሪካ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ኢኮኖሚዎች ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም።
በታምራት ቢሻው