በወንዞችና በወንዝ ዳርቻዎች በካይ ቆሻሻን የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦች 550 ሺህ ብር ተቀጡ

You are currently viewing በወንዞችና በወንዝ ዳርቻዎች በካይ ቆሻሻን የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦች 550 ሺህ ብር ተቀጡ

AMN ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም

በወንዞችና በወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻን የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦች 550 ሺህ ብር መቀጣታቸዉን የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 መሀሪ እምነ በረድ ፋብሪካ ቆሻሻን በወንዝ ዳርቻ በመድፋቱ 300 ሺህ ብር ሲቀጣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረደ 12 ሰቨን ዲ የምግብ ፋብሪካ የድርጅቱን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ባለመያዝ እና አካባቢዉን ባለማፅዳቱ 100 ሺህ ብር ቀጥቷል።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አንድ ግለሰብ የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቁ 150 ሺህ ብር አስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት እርምጃ መወሰዱን ባለስልጣኑ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review