በሲ ቢ ኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመጀመሪያ ሳምንት የተደረገው የሸገር ደርቢ በቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ለጊዮርጊስ አምበሉ አቤል ያለው ወሳኙን ግብ በስሙ አስመዝግቧል።
በጨዋታው 53ኛው ደቂቃ አካባቢ የኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ ዳላንድ ኢብራሂም አቤል ያለው ላይ በሰራው ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ ወጥቷል።
18ሺ የሚጠጋ ተመልካች በአዲስ አበባ ስታዲየም የታደመው ጨዋታ ብዙ የግብ ዕድል የተፈጠረበት አልነበረም።
በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተደረገ ሌላ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1ለ1 ተለያይተዋል።
ለፋሲል በረከት ይግዛው ፣ ለንግድ ባንክ ዘላለም አበበ ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ