የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከአለም አቀፉ የክትባቶች ጥምረት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር ጋር ተወያዩ

You are currently viewing የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከአለም አቀፉ የክትባቶች ጥምረት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር ጋር ተወያዩ
  • Post category:ጤና

AMN ጥቅምት 9/2018

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ከሚገኘዉ የአለም ባንክ እና አይኤምኤፍ አመታዊ ስብሰባዎች ጎን ለጎን ከአለም አቀፉ የክትባቶች ጥምረት ጋቪ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር ጋር በጤና ስርዓቶች ዙሪያ አጋርነታቸዉን ማጠናከር በሚችሉባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጥምረቱ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ለረጅም ጊዜ ላደረገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልፀዉ ክትባቱ የሀገሪቱን የጤና ስትራቴጂ ማዕከል ያደረገና በሰው ሃብት ልማት ዘርፍ ወሳኝ ድርሻ እንዳለዉ አመላክተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review