የትኛውም የምንሰራው ልማት በህብረተሰቡ ዘንድ ደስታና እርካታን ለመፍጠር ያለመ ነው ሲሉ የከንቲባ ፅህፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ ተናገሩ፡፡
የአዲስ አበባ ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደርና ቋሚ ኮሚቴ የከንቲባ ፅህፈት ቤት ስራን ገምግሟል፡፡
ምክር ቤቱ በከተማዋ የሚሰሩ ስራዎች ሀላፊነት በተሞላበትና ተጠያቂነት በሰፈነበት መልኩ እንዲፈጸሙ በተለያዩ ጊዜያት ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል።
በመሆኑም የአዲስ አበባ ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደርና ቋሚ ኮሚቴ የከንቲባ ፅህፈት ቤት ስራን ገምግሟል፡፡
በግምገማው ከቋሚ ኮሚቴ አባላት ለተነሱ ጉዳዮች ማብራሪያ የሰጡት የከንቲባ ፅህፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ፤ የህዝቡን አቤቱታና ቅሬታ በመመለስ የምንሰራው ስራና ልማት በህብረተሰቡ ዘንድ ደስታና እርካታን ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል በተለያዩ ዘርፎች የስራ እድል መፍጠር ነው ያሉት አቶ ጥላሁን፤ ይህ ተግባርም ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡
በአዲስ አበባ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ለሌሎች ሀገራት ዜጎች በተገቢው መንገድ ለማሳወቅና አዲስ አበባን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በስፋት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ አቶ ጥላሁን ገልፀዋል፡፡
እንደ ከተማ አስተዳደር የተሰሩ ተግባራት የተሻለ የኑሮ አካባቢን በመፍጠር የኑሮ ጫናን የሚያቀሉ ተግባራት መከናዎናቸውን መገምገሙን የፍትህና መልካም አስተዳደርና ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር መሀመድ ጀማል ተናግረዋል፡፡
በንጉሱ በቃሉ