የሶፍ ኡመር ዋሻ ፕሮጀክት ከተለመደው ውጭ በአዲስ እይታ የሚያይ መሪ እንዳለን ያየንበት ነው ሲሉ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል።
በቀደሙት ጊዜያት ስለ ስፍራው የነበራቸውን አመለካከት ሲገልጹም፤ የባሌ ተራሮችን በቀይ ቀበሮ እና በስንዴ ምርት እንጂ እንደዚህ ጸጋ የተትረፈረፈበት መሆኑን አናቅም ነበር ብለዋል።
የአሁኑ መገለጥ ደግሞ ከተለመደው ውጭ ወጣ አድርጎ በአዲስ እይታ የሚያይ መሪ እንዳለን ያመላከተ ነው ሲሉ አክለዋል።
በደቡብ እና በምስራቅ ሀገራችን ክፍል ያለውን ጸጋ ተገልጦ አይተናል አሁን ደግሞ የባሌን እያየን ነው ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ ጸጋችን መግለጡ ተፈጥሮን አርቆ ከተፈጥሮ ጋር ታርቆ መኖር እንደሚቻል ጠቋሚ ስለመሆኑም አንስተዋል።
ከባሌ ብቻ ወስዶ ኢትዮጵያን መቀለብ ይቻላል ያሉት አምባሳደር ሬድዋን አሁን የተፈጠረው አዲስ አይታ የት እንደነበርን ቀጣይም የት እንደምንደርስ አመላካች ነው ብለዋል።
በ ፍሬሕይወት ብርሃኑ