የተደበቁ ሀብቶችን ማየት የሚችል እይታና ለመፈፀም የሚያስችል አቅም መፈጠሩ የሚያኮራ መሆኑን አምባሳደር ግርማ ብሩ ተናገሩ

You are currently viewing የተደበቁ ሀብቶችን ማየት የሚችል እይታና ለመፈፀም የሚያስችል አቅም መፈጠሩ የሚያኮራ መሆኑን አምባሳደር ግርማ ብሩ ተናገሩ

AMN – ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

የተደበቁ ሀብቶችን ማየት የሚችል እይታና ለመፈፀም የሚያስችል አቅም መፈጠሩ የሚያኮራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ ተናግረዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ እና በስራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር በውቡ ሶፍ ኡመር ዋሻ ውይይት አድርገዋል።

የሶፍ ኡመር ዋሻ ከዚህ ቀደም አብረን ልንውል የማንችል ሰዎች የተሰባሰብንበት እና ሀሳብ የተቀያየርንበት ቦታ ነው ያሉት አማካሪው አምባሳደር ግርማ፤ ስፍራው በተፈጥሮ ሀብት እና በቱሪዝም መስህብ ተደብቆ የኖረ በመሆኑ በብዙ የሚያስቆጭ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከደኑ እና የመሬት አቀማመጡ ባሻገር በሁለቱ የባሌ ዞኖች ከ360 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ለዱር እንስሳት መመደብ መቻል ለዘርፉ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል።

‎በአጠቃላይ የተሰሩ ስራዎች ሲታዩ አካባቢው ካለው ሀብት ጋር ሲታይ ብዙ እንደሚቀረው መገንዘባቸውንም አመላክተዋል ።

‎ይሁን እንጂ ይህንን ለማየት የሚችል እይታና ለመፈፀም የሚያስችል አቅም መፈጠሩ የሚያኮራ እና የተደሰቱበት መሆኑን ነው አምባሳደሩ የተናገሩት።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review