የመደመር መንግስት መጽሐፍ ያለፈ ታሪካችንን ከአሁኑ ጋር ያሰናሰለ እና የወደፊት አቅጣጫን ያመላከተ መሆኑን ምሁራን ገለጹ

You are currently viewing የመደመር መንግስት መጽሐፍ ያለፈ ታሪካችንን ከአሁኑ ጋር ያሰናሰለ እና የወደፊት አቅጣጫን ያመላከተ መሆኑን ምሁራን ገለጹ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN- ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም

የመደመር መንግስት መጽሐፍ ያለፈ ታሪካችንን ከአሁኑ ጋር ያሰናሰለ እና የወደፊት አቅጣጫን ያመላከተ መሆኑን ምሁራን ገለጹ፡፡

ከተለያዩ የመንገግስት ተቋማት የተዉጣጡ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በመደመር መንግስት መጽሐፍ ላይ በከንቲባ ጽሕፈት ቤት የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የመደመር መንግስት መጽሐፍ ያለፈ ታሪካችንን ከአሁኑ ጋር ያሰናሰለ እና የወደፊት አቅጣጫን ያመላከተ ነዉ ሲሉ ምሁራን በዉይይት መድረኩ አንስተዋል፡፡

በተለይ በጊዜ አጠቃቀም ውስንነት ምክንያት የገጠመ ችግርን በመተንተን የበለጸገች ሀገርን ለትውልድ ለማስረከብ ካለፉ ጉድለቶች ቁጭትን በመሰነቅ በምን ፍጥነትና ፈጠራ መጓዝ እንደሚገባ የሚያሳይ ነው ተብሏል።

በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የገጠሙ አጠቃላይ ስብራቶችን በመጠገን፣ በቀጣይ ሀገሪቱ አሁን ካለው ዓለም እኩል መሰለፍ የምትችልበትን መንገድ የሚያመላክት መሆኑም ተመላክቷል።

በዉይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review