የፈረንሳይ ቡጉዌስ ከተማ ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እንዲሁም ታሪካዊ ስፍራዎችን ጎበኙ

You are currently viewing የፈረንሳይ ቡጉዌስ ከተማ ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እንዲሁም ታሪካዊ ስፍራዎችን ጎበኙ

AMN ጥቅምት 13/2018

በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ከተማዋን ውብ ከማድረግ ባሻገር ብክለትን ከመከላከል አንፃር የሚደነቅ መሆኑን በአዲስ አበባ ጉብኝት ያደረጉ የፈረንሳይ ቡጉዌስ ከተማ ልዑካን ቡድን ተናገሩ፡፡

ልዑካን ቡድኑ የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እንዲሁም ታሪካዊ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል።

በከንቲባ ሊዮኔዳስ ሰርጌ፣ ምክትል ከንቲባ ሚስተር ዣን ሉክ ኤሪክ ኩዴይራት እና ሌሎች የከተማዋ ባለስልጣናት የተመራውን የቡግዌስ ከተማ የልዑካን ቡድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በከተማ እየተከናወነ ያለውን የልማት ስራ አስጎብኝቷል።

በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ከተማዋን ውብ ከማድረግ ባሻገር ብክለትን ከመከላከል አንፃር የሚደነቅ መሆኑንም ልዑካን ቡድኑ ገልጿል።

አዲስ አበባ እያከናወነች ያለውን የልማት ስራ እንደሚደግፍ እና እንደ ትምህርት ባሉ ዘርፎች በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳላቸውም የቡግዌስ ከተማ ልዑካን ተናግረዋል ።

የልዑካን ቡድኑ በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት በብጉየስ እና በድሬዳዋ መካከል ያለውን የእህትማማች ከተማ አጋርነት ለማጠናከር ነው ወደ ኢትዮጵያ ለስራ ጉብኝት የመጣው።

በአሰግድ ኪዳነማርያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review