አፍሪካዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ 30 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት በማካበት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆኑ

You are currently viewing አፍሪካዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ 30 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት በማካበት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆኑ
  • Post category:አፍሪካ

AMN – ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም

ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ 30 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሀብት በማካባት የመጀመሪያዊ አፍሪካዊው መሆናቸውን ብሉምበርግ አስነብቧል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በብሉምበርግ የቢሊየነሮች ማውጫ ላይ በ29.6 ቢሊዮን ዶላር ተመዝግበው የነበሩት ዳንጎቴ፤ አሁን ደግሞ 30 ቢሊዮን ዶላርን በመድፈን የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነዋል።

ዳንጎቴ በኮቲዲቯር ከአቢጃን ከተማ 30 ኪሜ ርቀት ላይ የተመረቀው የ160 ሚሊዮን የስሚንቶ ማምረቻ ፋብሪካ ስራ መጀመር ለሳምንታዊው ገቢያቸው መጨመር ምክንያት ነው ተብሏል።

በዓመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስሚንቶ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው ከናይጄሪያ ውጭ የተገነባ የመጀመሪያው ግዙፍ ፋብሪካ መሆኑ ተገልጿል።

አሊኮ ዳንጎቴ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 55 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም ያላቸው የስሚንቶ ፋብሪካዎች በ11 የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አቋቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በነዳጅ ማጣሪያ ዘርፍ ያላቸውን አቅም በዕጥፍ በመጨመር በቀን 1.4 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ለገበያ የማቅረብ ውጥን እንዳላቸው በቅርቡ ይፋ አድርገዋል።

በ2024፤ 9 ቢሊዮን የተጣራ ሀብት የነበራቸው አፍሪካዊው ቱጃር ዳንጎቴ፤ 10.3 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት ባስመዘገቡት ደቡብ አፍሪካዊው ባለሀብት ዮሀን ሩፐርት በአፍሪካ የአንደኝነቱን ደረጃ ተነጥቀው ነበር።

ሆኖም በዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ የነበራቸውን ትርፍ በማሳደግ ሀብታቸውን ወደ 20.4 ቢሊዮን ዶላር ከፍ አድርገው ደረጃውን መልሰው ተቆጣጥረዋል።

በዳዊት በሪሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review