የጣና ፎረም ነገ በባህር ዳር ከተማ ይጀመራል

You are currently viewing የጣና ፎረም ነገ በባህር ዳር ከተማ ይጀመራል
  • Post category:ወቅታዊ

AMN ጥቅምት 13/2018

ነገ በሚጀምረው በ11ኛው የጣና ፎረም ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት ልዑካን ወደ ባህርዳር እየገቡ ይገኛሉ።

አፍሪካውያን መሪዎችን እና ባለድርሻ አካላትን በአሕጉራዊ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በማወያየት ዘላቂ መፍትሔዎችን ለመቀየስ አልሞ የሚካሄደው 11ኛው የጣና የሰላም እና ደህንነት መድረክ ከጥቅምት 14 እስከ 16 ቀን 2018 ዓ ቀን ዓ.ም በባህር ዳር እና አዲስ አበባ ይካሄዳል።

የልዑካን ቡድኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ፣ የባህር ዳር ከንቲባ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚመክረውን 11ኛው የጣና ፎረም ለመታደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት እንግዶች ባህርዳር ከተማ ገብተዋል።

የጣና ፎረም ከነገ ጥቅምት 14 ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ መካሄድ ይጀምራል።

በአፍሪካ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚመክረው 11ኛው ጣና ፎረም ጥቅምት 15 እና 16 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review