በአዲሱ አሰልጣኝ ሾን ዳይች እየተመራ የመጀመሪያ የዩሮፓ ሊግ ጨዋታውን ያደረው ኖቲንግሃም ፎረስት ፖርቶን 2ለ0 አሸንፏል።
ሞርጋን ጊብስ ኋይት እና ኢጎር ጄሱስ ሁለቱንም ግቦች በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።
አንጅ ፖስቴኮግሉን አሰናብተው ሾን ዳይችን ያመጡት ፎረስቶች የውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ የዩሮፓ ሊግ ድላቸው ሆኗል።
በአጠቃላይ በአውሮፓ ውድድር ጨዋታ ሲያሸንፉ ከ29 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
በሌሎች ጨዋታዎች በሮቢን ቫንፐርሲ የሚመራው ፌይኖርድ ፓናታኒያኮስን 3ለ1 አሸንፏል።
ሮማ በሜዳው በቪክቶሪያ ፕሌዝን 2ለ1 ሲሸነፍ ፣ ሊል እና ፓኦክ ያደረጉት በግቦች የታጀበ ጨዋታ በፓኦክ 4ለ3 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በሌላ በኩል በዩሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ የቆጵሮሱን ክለብ ላርናካ የገጠመው ክሪስታል ፓላስ 1ለ0 ተሸንፏል።
በሸዋንግዛው ግርማ