የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት የጎንደር ከተማን ወደ ሕይወት መልሷቷል ሲሉ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።
ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የታሪካዊ ሥነ-ሕንፃዎች ጥበቃ እና እድሳት የሥነ-ሕንፃ እሴቶችን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ታላቅ የኢትዮጵያ ቤተ-መንግሥት የነበረው የጎንደር አብያተ መንግሥት በሚያምር እና የመነሻውን አርክቴክቸር በጠበቀ መልኩ ውብ ሆኖ መታደሱን ም ገልጸዋል።
አሁን ጎንደር ድሮ እና ዘንድሮን አጣምራ የያዘች ማራኪ እና የምታምር ከተማ መሆኗን ነው ፕሬዚዳንቱ የጠቀሱት።