የኢትዮጵያ ብልጽግና ህልም መሳካት አይቀሬነትን የሚያበስሩ አፈጻጸሞች በሁሉም ዘርፎች መታየታቸውን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ብልጽግና ህልም መሳካት አይቀሬነትን የሚያበስሩ አፈጻጸሞች በሁሉም ዘርፎች መታየታቸውን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ

AMN ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብልጽግና ህልም መሳካት አይቀሬነትን የሚያበስሩ አፈጻጸሞች በሁሉም ዘርፎች መታየታቸውን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ ከሚኒስትሮች ጋር በኮይሻ ግድብ አካሂደዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ከተስፋ ብርሀን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን ለመሸጋገር እንደ ሃገር የተቀመጠዉ ዕቅድ ተጨባጭ ዉጤት እያስመዘገበ መሆኑን በመግለጽ ኢኮኖሚው የሚመራበት እና የሚቃኝበት ዕሳቤ ምን ያክል ትክክለኛ እና ውጤታማ እንደሆነ ማሳያ ነዉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብልጽግና ህልም መሳካት አይቀሬነትን የሚያበስሩ አፈጻጸሞች በሁሉም ዘርፎች መታየታቸውንም አውስተዋል።

የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ አቅጣጫዎች ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅ ሀብት በሙሉ አሟጣ በመጠቀም ወደ ብልጽግና ለመሸጋገር የምታደርገውን ጉዞ ያጠረ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል።

ግብርናው እና የኢንደስትሪው ዘርፍ ተሳስሮ መጓዙ እንዲሁም የማዕድኑ ዘርፍ ከዲጂታል ኢኮኖሚው ጋር ያለው ትስስር የላቀ መሆኑ ሀገሪቱ ያላትን ሁሉንም አቅሞች ተጠቅማ የመበልጸግ ህልሟን ማሳካት እንደምትችል ተጨባጭ ዉጤት ያሳየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከኢኮኖሚ እድገት አኳያ እድገቱ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በለፋዉ እና በሰራዉ ልክ ሕይወቱን የሚቀይር መሆኑን አመላክተዋል።

በትላልቅ ፕሮጀክቶች እየመጣ ያለዉ የኢኮኖሚ ለውጥ ተደራሽነቱ አብዛኛውን ያካተተ እና ጥራት ያለው መሆኑንም ገልጸዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ፣ የወልመል መስኖ ልማት ግድብ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ እና ሌሎቹም ፕሮጀክቶች አጠቃላይ ከድህነት ለመላቀቅ የምናደርገውን ትግል የሚያፋጥኑ ናቸዉ ብለዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review