መከላከያ ሰራዊት የሉዓላዊነታችን እና የአንድነታችን ጠባቂ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ገልጸዋል።
118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን “የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት” በሚል መሪ ሀሳብ በቢሾፍቱ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል በተለያዩ መርሐ- ግብሮች እየተከበረ ነው።
በመርሐ-ግብሩም የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ መከላከያ ሰራዊት የሉዓላዊነታችን እና የአንድነታችን ጠባቂ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ሰራዊቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ነጻነትን እና ክብርን ማስጠበቅ የቻለው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፣ በዚህ ትውልድም ይቀጥላል የኢትዮጵያ ብልጽግናም ይሳካል ብለዋል።
ይህ ሰራዊት የብሄራዊ መንፈስ ነጸብራቃችን እና ዋስትናችን ነው ሲሉም አክለዋል።
በተለያዩ ወቅቶች ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ ለመድፈር ቢሞከርም አልተሳካም ያሉት ሚኒስትሯ፣ ሰራዊታችንን የሚቋቋም ጠላት አልነበረም፣ አይኖርምም በማለት ነው የገለጹት።
በዳንኤል መላኩ