ባሳካነው ውጤት ሳንገደብ ወደ ሌላኛው ግባችን ለመድረስ በትኩረት መገስገስ ይጠበቅብናል ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል::
ፕሮጀክቶችን መከታተል እና መረዳት ለውጥኑ መትጋት እና እስከ ፍጻሜ መትጋት ለቀጣይ ስኬት እንደሚያበቃም አመላክተዋል።
የኮይሻ ግድብ እና ሌሎችም የደረሱበት ደረጀ ፣ ጨረስን ብሎ መቆም ሳይሆን ሌላ ሥራ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ያረጋገጡበት መሆኑንም አንስተዋል።
በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ከዚህ በፊት ያለቁ እና ሌላ ቦታ ተመርተዉ ይመጡ የነበሩ ጥሬ እቃዎችን በራስ አቅም ማምረት መቻሉ ትክክለኛ አቅም ከመፍጠር ባሻገር ጊዜ እና ገንዘብ መቆጠብ ያስችላል ብለዋል።
ሙያተኞችን መፍጠር መቻላችን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣይ አህጉራዊ ስራዎች ባለሞያ ትውልድ እንድንፈጥር አስችሎናልም ብለዋል።
የኮይሻ ፕሮጀክት ሀገር ወዳድ ሰራተኞች በውስጡ መያዙ ብቻ ሳይሆን፣ አጠናቆ የማየት ምልክቶችን ያዩበት መሆኑን ጠቅሰዋል።
መፈጸም፣ ማድረግ፣ ቀጥሎም መፈለግ እንደሚገባና ይህንንም ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አስተውዬበታለሁም ሲሉ ሚኒስትሯ ገልፀዋል ።
በወርቅነህ አቢዮ