ኢትዮጵያዊቷ ቡዜ ድሪባ የፍራንክፈርት አሸናፊ ሆናለች።
የ2023 የቶሮንቶ ማራቶን አሸናፊዋ ቡዜ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:19:34 ሰዓት ፈጅቶባታል። የግል ምርጥ ሰዓቷ ሆኖም ተመዝግቦላታል።
በሌላ በኩል አትሌት በላይ አስፋው የ42ኛው የፍራንክፈርት ማራቶን አሸናፊ ሆኗል አትሌቱ ርቀቱን ለመጨረስ 2:06:16 ሰዓት ፈጅቶበታል።
በላይ የፍራንክፈርት ማራቶንን ያሸነፈ 6ኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆኗል። ሌሎች ኢትዮጵያውያን ተሬሳ ቤኩማ እና ሹራ ቂጣታ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።