43ኛዉ እና 2ኛዉ የጆርካ አዲስ አበባ ሀገር አቋራጭ ዉድድር በጃን ሜዳ ተካሄደ ::
ከ1ኛ እና 2ኛ ዲቪዚዮን ክለቦች ከሁለቱም ጾታ የተዉጣጡ 480 አትሌቶች ተካፋይ ሁነዉበታል፡፡
በታዳጊ ሴቶች እና በወጣት ወንዶች ኢኮስኮ አትሌቲክስ ክለብ በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ በአዋቂ ወንዶች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በሴቶች ፌድራል ፖሊስ በቀዳሚነት አጠናቀዋል፡፡
ተሳታፊ አትሌቶች እና አሰልጣኞች ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ውድድሩ ጥሩ ፉክክር የተደረገበት እንደሆነ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ በበኩሉ ተተኪ አትሌቶች እራሳቸዉን ያዩበት እና ለሀገር አቀፍ ዉድድር ዝግጅታቸዉን የገመገሙበት ነዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በአለማየሁ ሙሳ