ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በነገው ዕለት ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በነገው ዕለት ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።

በዚህ መደበኛ ስብሰባ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዕለቱ በሚካሄደው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ መጠቆሙን ከምክር ቤቱ ማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review