ሁለት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በእጩነት ቀረቡ

You are currently viewing ሁለት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በእጩነት ቀረቡ

AMN-ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም

የዓለም አትሌቲክስ በ2025 የጎዳና ላይ ሩጫ ጥሩ ብቃት ያሳዩ እጩዎችን በሁለቱም ፆታ ይፋ አድርጓል። በወንዶች ዮሚፍ ቀጄልቻ በሴቶች ደግሞ ትዕግስት አሰፋ እጩ ውስጥ ተካተዋል።

ትዕግስት በለንደን ማራቶን በሴቶች ብቻ በተደረገ ውድድር የዓለም ክብረወሰን ማስመዝገቧ ይታወሳል። ወንዶች በአሯሯጭነት ባልተካተቱበት ውድድር አትሌቷ 2:15:50 ሰዓት መግባቷ አይዘነጋም።

አትሌት ትዕግስት በተጨማሪ በቶክዮ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን ለሀገሯ የብር ሜዳልያ አስገኝታለች። ዮሚፍ ቀጀልቻ በበኩሉ በ2025 በ5 እና በ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድሮችን ድል ማድረግ ችሏል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review