የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ሞስኮ ገቡ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ሞስኮ ገቡ

AMN-ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም

አፈ ጉባኤዋ ወደ ሩሲያዋ መዲና ያቀኑት በብሪክስ አባልና አጋር አገራት ዋና ከተማ ምክር ቤቶች ዓለም አቀፍ ጥምረት 2025 ጉባኤ ለመሳተፍ መሆኑን ምክርቤቱ በላከልን መረጃ ጠቅሷል።

በጉባኤው የብሪክስ አገራት ርዕሰ መዲና የሕዝብ ምክር ቤቶች በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል።

አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድርም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትን ወክለው የመግባቢያ ስምምነቱን እንደሚፈርሙና ምክር ቤቱ ጥምረቱን በይፋ ተቀላቅሎ ለጋራ ግቦች ስኬት የበከሉን ድርሻ ለማበርከት ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚገልጹ እንደሙጠበቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review