ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።
በዚህ ስብሰባ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በስብሰባው ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
የስብሰባው ሙሉ ሂደትም በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ እንደሚተላለፍ ምክር ቤቱ አስታውቋል።
የትዉልድ ድምጽ የሆነዉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በዲጂታል ሚዲያ አማራጮቹ ጭምር የምክር ቤቱን ዉሎ በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ ያስተላልፋል።