የግብርናው ዘርፍ ባለፈው ዓመት 7.3 በመቶ ዕድገት አምጥቷል

You are currently viewing የግብርናው ዘርፍ ባለፈው ዓመት 7.3 በመቶ ዕድገት አምጥቷል

AMN – ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

የግርናው ዘርፍ ባለፈው ዓመት 7.3 በመቶ ዕድገት እንዳመጣ እና ከአምና አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት ውስጥም ግብርና 2.3 በመቶ ድርሻ እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ኢኮኖሚን በተመለከተ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸውም፤ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን አንስተዋል።

ለአብነትም ግብርና ብቻውን የ7.3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት።

የግርናው ዘርፍ ባለፈው ዓመት 7.3 በመቶ ዕድገት እንዳመጣ እና ከአምና አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት ውስጥም 2.3 በመቶ ድርሻ እንዳለው ነው ያመላከቱት፡፡

ይህም በሪፎርሙ ማግስት በ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሩዝ ምርት 1.5 ሚሊዮን ኩንታል ከነበረበት ባለፈው ዓመት 63 ሚሊዮን ኩንታል ማምረት መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

ስንዴን በተመለከተም በለውጡ ማግስት ኢትዮጵያ 47 ሚሊዮን ኩንታል ታመርት የነበረ ሲሆን፣ መንግስት በየዓመቱ የ1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ከውጭ እንደሚያስገባ እና ክልሎችም የስንዴ ኮታ እንደ በጀት ይጠብቁ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ይሁንና የስንዴ ምርትን ከለውጡ በፊት ከነበረበት 47 ሚሊየን ኩንታል በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ280 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review