ታንዛኒያ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

You are currently viewing ታንዛኒያ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

AMN-ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሁለተኛ ዙር በደርሶ መልስ ጨዋታ ኢትዮጵያን የረታችው ታንዛኒያ ለአፍሪካ ዋንጫ አልፋለች።

በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው የመልስ ጨዋታ ታንዛኒያ ኢትዮጵያን 1ለ0 አሸንፋለች።

በሜዳዋ 2ለ0 ማሸነፍ የቻለችው ታንዛኒያ በድምር ውጤት 3ለ0 በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን አረጋግጣለች።

ከ14 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ መድረክ የመመለስ እድላቸው ለጊዜው ያልተሳካላቸው ሉሲዎቹ ሌላ ማጣሪያ ሊያደርጉ ይችላሉ።

ተሳታፊ ሀገራትን ከ12 ወደ 16 የማሳደግ እቅድ ያለው ካፍ በሁለተኛው ዙር የተሸነፉ ሀገራት ወደፊት በሚገለፅ የማጣሪያ መንገድ አራት ብሔራዊ ቡድኖችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ካፍ በዚህ ዙሪያ በቅርቡ መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review