መንግስት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ እና የብዙሃኑን ድምጽ ለመስማት ዝግጁ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing መንግስት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ እና የብዙሃኑን ድምጽ ለመስማት ዝግጁ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN -ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

መንግሥት 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማከናወን እና የብዙሃኑን ድምጽ ለመስማት ዝግጁ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ፣ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ አንዳንድ ፍላጎቶች እንደሚታዩበት በማመላከት፤ እስካሁን በኢትዮጵያ ከተካሄዱት ምርጫዎች የተሻለ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

መንግሥትም ምርጫውን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማካሄድ፣ የብዙሃኑን ድምፅ ለመስማት በቂ አቅም እና ዝግጁነት እንዳለውና ለዚህም በኃላፊነት እንደሚሠራ አጽኖት ሰጥተዋል።

የፖለቲካ ፖርቲ አባላትም ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ድምጾች ለመስማት ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review