በኬንያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ

You are currently viewing በኬንያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ

AMN – ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም

ኬንያ ውስጥ ቱሪስቶችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ተከስክሶ 11 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።

አነስተኛ የመንገደኞች አውሮፕላኑ ትናንት ኩዋሌ ከተባለው የኬንያ የባህር ዳርቻ ግዛት ተነስቶ ወደ ማሳኢ ማራ ጥብቅ ደን ብሔራዊ ፓርክ እያመራ በነበረበት ወቅት አደጋው መከሰቱን የአቪየሺን ባለስልጣናት ገልጸዋል።

​አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ከዲያኒ አየር ማረፊያ በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ኮረብታማና ደን በበዛበት አካባቢ መሆኑን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የኬንያ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ትስስር ገጾች አውሮፕላኑ በእሳት ተቃጥሎ እና ተበታትኖ የሚያሳዩ ምስሎችን እያሠራጩ ይገኛሉ።

በአደጋው በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ 10 አውሮፓውያን እና ኬንያዊ አብራሪ ሕይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ አስነብቧል ።

የአደጋው መንስኤ እስካሁን ባይታወቅም የሀገሪቱ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ሠራተኞች በአደጋው ስፍራ ያጋጠመውን ጉዳት እና የአደጋውን ምክንያት እየመረመሩ ነው ብሏል።

በዳዊት በሪሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review