የብልፅግና ፓርቲ ዓመታዊ ስልጠና ማካሄድ ጀመረ

You are currently viewing የብልፅግና ፓርቲ ዓመታዊ ስልጠና ማካሄድ ጀመረ

AMN – ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

የብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓመታዊ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ማካሄድ ጀምሯል።

ስልጠናው “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ሐሳብ ለሚቀጥሉት 10 ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል። ስልጠናው የአመራሩን ዕውቀት፣ ክኅሎትና ዐቅም የሚገነቡ ልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚቀርቡበት መሆኑም ተገልጿል።

በስልጠናው ከ2ሺህ በላይ ከፌዴራልና ከክልል የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች እንደሚሳተፉ ተጠቁሟል። ከስልጠናው በተጓዳኝ የተግባር የመስክ የልማት ሥራ ጉብኝቶች እንደሚካሄድም ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review