በተቋማት ውስጥ አገልግሎት የማይሰጡ የተከማቹ ንብረቶችን ማስወገድ ትኩረት ይፈልጋል

You are currently viewing በተቋማት ውስጥ አገልግሎት የማይሰጡ የተከማቹ ንብረቶችን ማስወገድ ትኩረት ይፈልጋል

AMN – ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

በተቋማት ውስጥ አገልግሎት የማይሰጡ የተከማቹ ንብረቶችን ማስወገድ አሁንም ትኩረት እንደሚፈልግ የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ገለጸ፡፡

”ጊዜን ማዕከል ያደረገ የንብረት አወጋገድ ለከተማችን እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች እና ሴክተር ተቋማት ተሳታፊዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ የሱፍ ኢብራሂም፤ በተቋማት ውስጥ አገልግሎት የማይሰጡ የተከማቹ ንብረቶችን ማስወገድ ላይ ተቋማት ትኩረት ሊሰጡ እና ኃላፊነታቸው ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማን የእድገት ደረጃ የሚመጥን፣ ወቅቱን የጠበቀ የንብረት ማስወገድ ማከናወን፣ ዘመናዊ የንብረት አስተዳደር መዘርጋት እና የንብረት ምዝገባ ማካሄድ እንደሚገባም አቶ የሱፍ ኢብራሂም ገልጸዋል።

የብረት ቁርጥራጭ እና አገልግሎት የማይሰጡ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በከተማዋ በ18 ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ሊወገድ የሚችል ንብረት መኖሩም በመድረኩ ተገልጿል።

አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን የማስወገድ ባህል እየዳበረ ቢሆንም አሁንም ትኩረት የሚሻ መሆኑም ተጠቅሷል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review