የሳይበር ፖሊሲን ተግባራዊ ባላደረጉ ተቋማት ላይ የማስፈፀሚያ አስገዳጅ ሕግ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡
እንደ ሀገር የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ትግበራ ላይ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የሳይበር ደህንነት ባለሙያ አቶ አየለ ሙሴ በተለይም ለAMN FM 96.3 ሬዲዮ ገለፁ።
ዘመኑ የዲጂታል እንደመሆኑ፣ መረጃ መንታፊዎች ኢላማ የሚያደርጉት አገርን ብቻ ሳይሆን ተቋማትንና ግለሰቦችንም ጭምር በመሆኑ ዘመኑን የዋጀ የመከላከል ሥራ ለመስራት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ከፍተኛ ሥራ እየሠራ መሆኑን አቶ አየለ ገልፀዋል፡፡
የችግሩን አሳሳቢነት ተረድቶ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲን እና ስትራቴጂን በተሟላ ሁኔታ ለማስተግበር እንዲቻልም አስገዳጅ ሕግ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።
የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ተረድቶ ከዚሁ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራስን ማብቃትና የሚመለከተው አካል የሚሰጠውን የግንዛቤ መረጃና ማስጠንቀቂያ መቀበልና መከተል እንደሚገባም ገልፀዋል።
በሽመልስ ታደሠ